top of page

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ አጋጥሞ የነበረውን ችግር ለተለዬ አጀንዳ ለማዋል የሚጠቀሙ አካላትን ዩኒቨርሲቲው አወገዘ፡፡

  • Writer: Ayalew-kuma
    Ayalew-kuma
  • Nov 11, 2019
  • 1 min read

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ 13 ተጠርጣዎች በቁጥጥ ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉንና የተወሰኑ ተማሪዎች መቁሰላቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተፈራ አስናቀ ለአብመድ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ከትናንት ጀምሮ በተረጋጋና በሠላማዊ ሁኔታ ይገኛል፤ ተማሪዎችም እንዲረጋጉ በየደረጃው ውይይቶች ተደርገዋል፤ ዛሬም እንደቀጠሉ ናቸው፡፡ የዩኒቨርሲቲውና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማት አባቶችም ተማሪዎችን እያወያዩና እያረጋጉ ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ለመመለሥ እየጣሩ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው እንዳመለከተውም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 13 ሰዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደ ነው፡፡ ድርጊቱ አሳዛኝና ያልተጠበቀ መሆኑን ያመለከቱት አቶ አስናቀ ‹‹አሁን በዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያው ግጭት በቀር ምንም ችግር አላጋጠመም፤ የወልድያ የሀገር ሽማግሌዎችም ሆስፒታል ሄደው የተጎዱትን ጠይቀዋል፤ ተማሪዎችንም ዛሬም እያወያዩ ነው›› ብለዋል፡፡ ድርጊቱን በፈፀሙት ላይ ተጣርቶ እርምጃ እንዲወሰድ ተማሪዎች መጠየቃቸውን ያስታወሱት አቶ አስናቀ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን 13 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራው መቀጠሉን አመልክተዋል፡፡ ከተማሪዎች ጋር ቀጣይ ውይይቶች መኖራቸውንም አመላክተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በማኅበራዊ ገጹ ክስተቱን ለተለዬ አጀንዳ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካላት ከድረጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ዜጎች እውነታውን እንዲረዱ ዩኒቨርሲቲው ተከታታይ መረጃ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post

Contact

+251978778960

©2018 by Political Ideas. Proudly created with Wix.com

bottom of page