top of page

ከ “ኬኛ ፖለቲካ” ጋር የሚደረገው ትግል መራራ ነው! አሸንፈኸውም እሸቱ አይጣፍጥም! (አቶ አሰማህኝ አስረስ) ====================

  • Writer: Ayalew-kuma
    Ayalew-kuma
  • Nov 11, 2019
  • 1 min read

ትናንት ወልድያ ዩኒቨርሲቲ መጠነኛ ግርግር ተከስቶ ወዲውኑ የጸጥታ ሀይሎች ገብተው ተረጋግቷል። የተወሰኑ ተማሪዎች መጠነኛ የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል።

ይህንን ግጭት ሌላ መልክ ለመስጠት እየሞከሩ ያሉት የ “ኬኛ ፖለቲከኞች” በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰው እንደ ከብት አጋድመው ያረዱ: በድንጋይ የወገሩ: በእሳት ያነደዱ የሰው አምሳል የሌላቸው አረመኔዎች ናቸው። በእነዚህ ጨካኞች ምክንያት ኢትዮጵያ ዝቅ ብላለች።

ባለፈው ሳምንት አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተፈጥሮ በአማራ ክልል ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደርሶ እንደነበር አታውቁምን? ለምን የዛኔ አልጮኻችሁም? በዚህ ወር ውስጥ አምቦ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ የተጎዱ የአማራ ተማሪዎች አልነበሩምን? ለምን የዛኔ አልተናገራችሁም?

የ “ኬኛ ፖለቲካ” ችግሩ ስግብግብነቱ ነው። የሰው ሁሉ ድርሻ የኔ ነው ማለቱ ነው። የኬኛ ፖለቲካ ችግሩ ምክንያታዊነት የሌለው ግብዝ መሆኑ ነው። በአገሩ እኔ ብቻ ልኑርበት ማለቱ ነው።

ከኬኛ ፖለቲካ ጋር የሚደረገው ትግል መራራ ነው! አሸንፈኸውም እሸቱ አይጣፍጥም!

AMS

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post

Contact

+251978778960

©2018 by Political Ideas. Proudly created with Wix.com

bottom of page